2 ተሰሎንቄ 3:16-18

2 ተሰሎንቄ 3:16-18 NASV

የሰላም ጌታ ራሱ በሁሉም ነገር ዘወትር ሰላም ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋራ ይሁን። ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍሁት እኔ ጳውሎስ ነኝ፤ የመልእክቶቼም ሁሉ መለያ ይህ ነው፤ አጻጻፌም እንደዚህ ነው። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋራ ይሁን።