2 ሳሙኤል 7:1-5

2 ሳሙኤል 7:1-5 NASV

ንጉሡ በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ ከተቀመጠና እግዚአብሔርም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ካሳረፈው በኋላ፣ ንጉሡ ነቢዩ ናታንን፣ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው። ናታንም፣ ንጉሡን “እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ስለ ሆነ፣ ያሰብኸውን ሁሉ አድርግ” ሲል መለሰለት። በዚያች ሌሊት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን እንዲህ ሲል መጣ፤ “ሂድና ባሪያዬን ዳዊትን፣ ‘እንዲህ ብለህ ንገረው፤ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ ነህን? በለው።