2 ሳሙኤል 22:47-50

2 ሳሙኤል 22:47-50 NASV

“እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን! አምላኬ የድነቴ ዐለት ከፍ ከፍ ይበል። በቀሌን የሚመልስልኝ፣ አሕዛብንም ከሥሬ የሚያስገዛልኝ እርሱ ነው፤ እርሱ ከጠላቶቼ እጅ ነጻ ያወጣኛል። አንተ ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፤ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም በመዝሙር እወድሳለሁ።