2 ነገሥት 5:1-5

2 ነገሥት 5:1-5 NASV

በዚህ ጊዜ ንዕማን የሶርያ ንጉሥ ጦር አዛዥ ነበረ፤ እግዚአብሔር በዚህ ሰው አማካይነት፣ ሶርያ ድልን እንድትጐናጸፍ ስላደረጋት በጌታው ዘንድ ታላቅና የተከበረ ሰው ነበር። ጀግና ወታደር ቢሆንም ለምጽ ወጥቶበት ነበር። አደጋ ጣዮች ከሶርያ ወጥተው፣ ከእስራኤል ምድር አንዲት ልጃገረድ ማረኩ፤ እርሷም የንዕማንን ሚስት ታገለግላት ነበር። እመቤቷንም፣ “ጌታዬ በሰማርያ ያለውን ነቢይ ሄዶ ቢያገኘው እኮ ከዚህ ቈዳ በሽታው ይፈውሰው ነበር” አለቻት። ንዕማንም ወደ ጌታው ሄዶ ከእስራኤል የመጣችው ልጃገረድ ያለችውን ነገረው። የሶርያም ንጉሥ፣ “በል እንግዲያው አሁኑኑ ሂድ፤ እኔም ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እጽፋለሁ” አለው፤ ስለዚህ ንዕማን ዐሥር መክሊት ብር፣ ስድስት ሺሕ ሰቅል ወርቅና ዐሥር ሙሉ ልብስ ይዞ ሄደ።