2 ነገሥት 25:27-30

2 ነገሥት 25:27-30 NASV

የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ ሰባተኛው ቀን ዮርማሮዴክ በባቢሎን በነገሠ በዓመቱ ዮአኪንን ከወህኒ ፈታው። በመልካምም ቃል አናገረው፤ ከርሱም ጋራ በባቢሎን በምርኮ ከነበሩት ነገሥታት ይልቅ ከፍ ባለ የክብር ቦታ አስቀመጠው። ዮአኪንም የእስር ቤት ልብሱን ጣለ፤ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ ከንጉሡ ማእድ ዘወትር ይመገብ ነበር፤ ንጉሡም ለዮአኪን እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ የዕለት ቀለቡን ይሰጠው ነበር።