2 ቆሮንቶስ 10:9-12

2 ቆሮንቶስ 10:9-12 NASV

በመልእክቶቼ የማስፈራራችሁ አይምሰላችሁ። አንዳንዶች፣ “መልእክቶቹ ከባድና ጠንካራ ናቸው፤ ነገር ግን ሰውነቱ ሲታይ ደካማ፣ ንግግሩም የተናቀ ነው” ይላሉ። እንዲህ የሚሉ ሰዎች በሩቅ ሆነን በመልእክታችን የምንናገረውን ሁሉ በቅርብ ሆነን በተግባራችን የምንገልጸውም እንደዚያው መሆኑን መገንዘብ አለባቸው። ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ሰዎች ጋራ ራሳችንን ልንመድብ ወይም ልናነጻጽር አንደፍርም፤ እነርሱ ራሳቸውን በራሳቸው ሲመዝኑና ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋራ ሲያነጻጽሩ አስተዋዮች አይደሉም።