እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ለነገሥታትና ለባለሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ ይኸውም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው። ይህ በእግዚአብሔር በአዳኛችን ፊት ደስ የሚያሰኝ ነው፤ እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል። አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ መካከለኛ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ራሱንም ለሰዎች ሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም በትክክለኛው ጊዜ ተመስክሮለታል። እኔም ለዚህ ነገር የምሥራች አብሣሪና ሐዋርያ እንዲሁም ለአሕዛብ የእውነተኛ እምነት አስተማሪ ሆኜ ተሾምሁ፤ እውነቱን እናገራለሁ፤ አልዋሽም። እንግዲህ ወንዶች በሁሉም ቦታ ያለ ቍጣና ያለ ክርክር የተቀደሱ እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ።
1 ጢሞቴዎስ 2 ያንብቡ
ያዳምጡ 1 ጢሞቴዎስ 2
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ጢሞቴዎስ 2:1-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች