1 ተሰሎንቄ 1:1-3

1 ተሰሎንቄ 1:1-3 NASV

ከጳውሎስ፣ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ፤ በእግዚአብሔር አብና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሆኑት ለተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን፤ ከእግዚአብሔር አብ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። በጸሎታችን እያስታወስናችሁ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ስለ ሁላችሁ እናመሰግናለን። ከእምነት የሆነውን ሥራችሁን፣ ከፍቅር የመነጨውን ድካማችሁንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ የተገኘውን ጽናታችሁን በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን።