ከጳውሎስ፣ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ፤ በእግዚአብሔር አብና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሆኑት ለተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን፤ ከእግዚአብሔር አብ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። በጸሎታችን እያስታወስናችሁ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ስለ ሁላችሁ እናመሰግናለን። ከእምነት የሆነውን ሥራችሁን፣ ከፍቅር የመነጨውን ድካማችሁንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ የተገኘውን ጽናታችሁን በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን። በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፣ እርሱ እንደ መረጣችሁ እናውቃለን፤ ምክንያቱም ወንጌላችን ወደ እናንተ የመጣው በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ፣ በብዙም መረዳት እንጂ በቃል ብቻ አይደለም። ደግሞ ስለ እናንተ ስንል በመካከላችሁ እንዴት እንደ ኖርን ታውቃላችሁ። እናንተ እኛንና ጌታን መስላችኋል፤ ምንም እንኳ ብርቱ መከራ ቢደርስባችሁም፣ ቃሉን በመንፈስ ቅዱስ ደስታ ተቀብላችኋል። ከዚህም የተነሣ በመቄዶንያና በአካይያ ለሚገኙ ምእመናን መልካም ምሳሌ ሆናችኋል። የጌታ ቃል ከእናንተ ወጥቶ በመቄዶንያና በአካይያ መሰማቱ ብቻ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ያላችሁ እምነት በሁሉ ቦታ ታውቋል፤ ስለዚህ እኛ በዚህ ጕዳይ ላይ ምንም መናገር አያስፈልገንም፤ በእንዴት ያለ አቀባበል እንደ ተቀበላችሁንና ሕያውና እውነተኛ የሆነውን አምላክ ለማገልገል ከጣዖታት ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደ ተመለሳችሁ እነርሱ ራሳቸው ይናገራሉ፤ ደግሞም ከሙታን ያስነሣውንና ከሰማይ የሚመጣውን ልጁን፣ ከሚመጣውም ቍጣ የሚያድነንን ኢየሱስን እንዴት እንደምትጠባበቁ ይናገራሉ።
1 ተሰሎንቄ 1 ያንብቡ
ያዳምጡ 1 ተሰሎንቄ 1
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ተሰሎንቄ 1:1-10
18 ቀናት
ሐዋርያው ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋርያት ሥራ 14:22) ይላል። የሐዋርያት ሥራን ማንበብ ወይም በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖችን ምስክርነት መስማት፣ የዚህን ቃል እውነት አረጋግጠዋል። አማኞች ተቃውሞ እና ስደት ይደርስባቸዋል። ምናልባት እርሶም መከራ አጋጥሞት ይሆናል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ፣ ልናበረታታዎት እና በመከራን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ማስተማር እንፈልጋለን።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች