ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፤ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ይለኛልና። “እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለም፤ ከአንተም በቀር ሌላ የለም፤ እንደ አምላካችን ያለ ዐለት የለም። “ይህን ያህል በመታበይ አትናገሩ፤ እንዲህ ያለውም የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፤ ሥራም ሁሉ በርሱ ይመዘናል። “የኀያላን ቀስቶች ተሰባብረዋል፤ ደካሞች ግን በኀይል ታጥቀዋል። ጠግበው የነበሩ ለእንጀራ ሲሉ ተገዙ፤ ተርበው የነበሩ ግን እንጀራ ጠገቡ፤ መካኒቱ ሰባት ልጆች ወልዳለች፤ ብዙ ወንዶች ልጆች ወልዳ የነበረችው ግን መከነች። “እግዚአብሔር ይገድላል፤ ያድናልም፤ ወደ መቃብር ያወርዳል፤ ያወጣልም። እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል። እርሱ ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ከመኳንንቱ ጋራ ያስቀምጣቸዋል፤ የክብር ዙፋንም ያወርሳቸዋል። “የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፣ ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጓል። እርሱ የታማኝ አገልጋዮቹን እግር ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ይጣላሉ። “ሰው በኀይሉ ድል አያደርግም፤ ከእግዚአብሔር ጋራ የሚጣሉ ይደቃሉ፤ እርሱ ከሰማይ ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል። “ለንጉሡ ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።” ከዚያ በኋላ ሕልቃና ወደ ቤቱ ወደ ራማ ሄደ፤ ብላቴናው ግን በካህኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።
1 ሳሙኤል 2 ያንብቡ
ያዳምጡ 1 ሳሙኤል 2
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ሳሙኤል 2:1-11
9 ቀናት
የመጀመሪያው የሳሙኤል መጽሐፍ የእስራኤላዊት ሴት የሆነችውን የሐናን ታሪክ ይዘግባል። የሕይወቷ ሁኔታ ያስጎነበሳት እና ተስፋ አስቆራጭ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እሷን ምሳሌ የምትሆን ፈሪሃ አምላክ ያላት ሴት አድርጎ ይገልጻታል። ይህ የንባብ እቅድ የሐናን የህይወት ታሪክ ለራሳችን ህይወት እንደ ምሳሌ ይወስደዋል። ከእኛ ጋር ያንብቡ።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች