መልካም ነገር ለማድረግ ብትቀኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራ ቢደርስባችሁ ብፁዓን ናችሁ፤ “ዛቻቸውን አትፍሩ፤ አትታወኩም።” ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤ በክርስቶስ ያላችሁን መልካም ጠባይ አክፋፍተው የሚናገሩ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ። የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ከሆነ፣ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል፤
1 ጴጥሮስ 3 ያንብቡ
ያዳምጡ 1 ጴጥሮስ 3
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ጴጥሮስ 3:13-17
5 ቀናት
ተስፋ ተኮር በሆነው ደብዳቤው ለመጀመሪያዋ ክፍለ ዘመን ቤተ-ክርስቲያን ጴጥሮስ በማመን፣ በመታዘዝ እና ፍርድና መከራ ሲገጥመን ፀንተን እንድንቆም ያበረታናል፡፡ ይህን የሚያሳስበን ምክንያት ደግሞ በክርስቶስ ማን እንደሆንን፣ ቅዱስ የሆነውን ኑሮ እንኖር ዘንድ ኃይል የሆነልንና ወደፊት ዘላለምን ለመውረስ የምንችል ነን በማለት ነው፡፡
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች