ወዳጆች ሆይ፤ በዚህ ዓለም እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት እንድትርቁ እለምናችኋለሁ። ምንም እንኳ ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል በመልካም ሕይወት ኑሩ። ስለ ጌታ ብላችሁ ለምድራዊ ባለሥልጣን ሁሉ ተገዙ፤ የበላይ ባለሥልጣን ስለ ሆነ ለንጉሥ ቢሆን፣ ወይም ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣትና በጎ አድራጊዎችን ለማመስገን እርሱ ለሾማቸው ገዦች ታዘዙ፤ ምክንያቱም፣ መልካም በማድረግ የአላዋቂዎችን ከንቱ ንግግር ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። እንደ እግዚአብሔር ባሮች ሆናችሁ በነጻነት ኑሩ እንጂ ነጻነታችሁን የክፋት መሸፈኛ አታድርጉት። ለሰው ሁሉ ተገቢውን አክብሮት ስጡ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።
1 ጴጥሮስ 2 ያንብቡ
ያዳምጡ 1 ጴጥሮስ 2
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ጴጥሮስ 2:11-17
5 ቀናት
ተስፋ ተኮር በሆነው ደብዳቤው ለመጀመሪያዋ ክፍለ ዘመን ቤተ-ክርስቲያን ጴጥሮስ በማመን፣ በመታዘዝ እና ፍርድና መከራ ሲገጥመን ፀንተን እንድንቆም ያበረታናል፡፡ ይህን የሚያሳስበን ምክንያት ደግሞ በክርስቶስ ማን እንደሆንን፣ ቅዱስ የሆነውን ኑሮ እንኖር ዘንድ ኃይል የሆነልንና ወደፊት ዘላለምን ለመውረስ የምንችል ነን በማለት ነው፡፡
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች