የዖምሪ ልጅ አክዓብ ከርሱ አስቀድሞ ከነበሩት ሁሉ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ። የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓምን ኀጢአት እንደ ቀላል ነገር ከመቍጠሩም በላይ የሲዶናውያንን ንጉሥ የኤትበኣልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በኣልን አመለከ፤ ሰገደለትም። ሰማርያ ላይ በሠራውም የበኣል ቤተ ጣዖት ለበኣል መሠዊያ አቆመለት። ደግሞም አክዓብ የአሼራን ምስል ዐምድ በማቆም ከርሱ በፊት ከነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ይልቅ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለቍጣ የሚያነሣሣ ድርጊት ፈጸመ። የቤቴል ሰው አኪኤል፣ በአክዓብ ዘመን ኢያሪኮን መልሶ ሠራት። እግዚአብሔር በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካይነት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ መሠረቷን ሲያኖር በኵር ልጁ አቢሮን ሞተ፤ የቅጽር በሮቿንም በሚሠራበት ጊዜ የመጨረሻው ልጁ ሠጉብ ሞተ።
1 ነገሥት 16 ያንብቡ
ያዳምጡ 1 ነገሥት 16
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ነገሥት 16:30-34
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች