1 ነገሥት 10:6-9

1 ነገሥት 10:6-9 NASV

ንጉሡንም እንዲህ አለችው፤ “ስለ ተናገርሃቸው ነገሮችና ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት እውነት ነው፤ ይሁን እንጂ፣ መጥቼ እነዚህን ነገሮች በዐይኔ እስካይ ድረስ የተነገረኝን አላመንሁም ነበር፤ በርግጥ ግማሹ እንኳ አልተነገረኝም፤ ጥበብህና ብልጽግናህ ከሰማሁት እጅግ ይልቃል። ሰዎችህ እንዴት ብፁዓን ናቸው! ዘወትር በፊትህ ቆመው ጥበብህን የሚሰሙ ሹማምትህ ምንኛ ብፁዓን ናቸው! በአንተ ደስ ተሰኝቶ በእስራኤል ዙፋን ላይ ያስቀመጠህ እግዚአብሔር አምላክህ ቡሩክ ይሁን፤ እግዚአብሔር በዘላለም ፍቅሩም እስራኤልን ከመውደዱ የተነሣ፣ ፍትሕና ጽድቅ እንዲሰፍን አንተን ንጉሥ አደረገህ።”

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}