1 ዮሐንስ 2:20-27

1 ዮሐንስ 2:20-27 NASV

እናንተ ግን ከርሱ፣ ከቅዱሱ ቅባት አላችሁና፣ ሁላችሁም እውነቱን ታውቃላችሁ። ለእናንተ የምጽፍላችሁ እውነቱን ስለማታውቁት አይደለም፤ ነገር ግን ስለምታውቁት እና ምንም ውሸት ከእውነቱ ስላልሆነ ነው። ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ሐሰተኛ ማነው? ይህ አብንና ወልድን የሚክደው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው። ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ የለውም፤ ወልድን የሚያምን ሁሉ አብም አለው። ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ውስጥ ይኑር፤ ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ውስጥ ቢኖር፣ እናንተም በወልድና በአብ ትኖራላችሁ። ይህ እርሱ የሰጠን ተስፋ የዘላለም ሕይወት ነው። ስለሚያስቷችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ። እናንተ ግን ከርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በውስጣችሁ ይኖራልና ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልግም፤ ነገር ግን የርሱ ቅባት ስለ ሁሉም ነገር፣ እውነተኛ የሆነውን እና ሐሰት ያልሆነው እናንተን እንደሚያስተምር፣ እናንተንም እንዳስተማራችሁ በርሱ ኑሩ።