1 ዜና መዋዕል 7:13-40

1 ዜና መዋዕል 7:13-40 NASV

የንፍታሌም ወንዶች ልጆች፤ ያሕጽሔል፣ ጉኒ፣ ዬጽር፣ ሺሌም፤ እነዚህ የባላ ዘሮች ናቸው። የምናሴ ዘሮች፤ ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት ልጁ አሥሪኤል ነው። እርሷም የገለዓድን አባት ማኪርን የወለደች ናት፤ ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ። እኅቱም መዓካ ትባል ነበር። ሌላው ዘሩ ሰለጰዓድ ሲሆን፣ እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት። የማኪር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፋሬስ አለችው። የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ። የኡላም ወንድ ልጅ፤ ባዳን፤ እነዚህ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው። እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣ አቢዔዝርንና ማሕላን ወለደች። የሸሚዳ ወንዶች ልጆች ደግሞ እነዚህ ነበሩ፤ አሒያን፣ ሴኬም፣ ሊቅሒ፣ አኒዓም። የኤፍሬም ዘሮች፤ ሱቱላ፣ ልጁ ባሬድ፣ ልጁ ታሐት፣ ልጁ ኤልዓዳ፣ ልጁ ታሐት፣ ልጁ ዛባድ፣ ልጁ ሹቱላ። ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣ የአገሩ ተወላጆች በሆኑት በጋት ሰዎች ተገደሉ። አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ ዘመዶቹም መጥተው አጽናኑት። ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪዓ አለው። ሴት ልጁ ስሟ ሲአራ ይባላል፤ እርሷም የታችኛውንና የላይኛውን ቤትሖሮንንና ኡዜንሼራን የተባሉትን ከተሞች የቈረቈረች ናት። ልጁ ፋፌ፣ ልጁ ሬሴፍ፣ ልጁ ቴላ፣ ልጁ ታሐን፣ ልጁ ለአዳን፣ ልጁ ዓሚሁድ፣ ልጁ ኤሊሳማ፣ ልጁ ነዌ፣ ልጁ ኢያሱ። ምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞች፣ በስተምሥራቅ ነዓራን፣ በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን፣ እንዲሁም ሴኬምንና መንደሮቿን፣ ከዚያም ዐልፎ ጋያንና መንደሮቿን በሙሉ ያጠቃልል ነበር። በምናሴም ወሰን ላይ ቤትሳን፣ ታዕናክ፣ መጊዶና ዶር ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። በእነዚህም መንደሮች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩ ነበር። የአሴር ወንዶች ልጆች፤ ዪምና፣ የሱዋ፣ የሱዊ፣ በሪዓ፤ እኅታቸውም ሤራሕ ትባል ነበር። የበሪዓ ወንዶች ልጆች፤ ሔቤርና የቢርዛዊት አባት መልኪኤል። ሔቤርም ያፍሌጥን፣ ሳሜርን፣ ኮታምንና እኅታቸውን ሶላን ወለደ። የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች፤ ፋሴክ፣ ቢምሃል፣ ዓሲት፤ የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ። የሳሜር ወንዶች ልጆች፤ አኪ፣ ሮኦጋ፣ ይሑባ፣ አራም። የወንድሙ የኤላም ወንዶች ልጆች፤ ጾፋ፣ ዪምና፣ ሰሌስ፣ ዓማል። የጾፋ ወንዶች ልጆች፤ ሱዋ፣ ሐርኔፍር፣ ሦጋል፣ ቤሪ፣ ዪምራ፣ ቤጴር፣ ሆድ፣ ሳማ፣ ሰሊሳ፣ ይትራን፣ ብኤራ። የዬቴር ወንዶች ልጆች፤ ዮሮኒ፣ ፊስጳ፣ አራ። የዑላ ወንዶች ልጆች፤ ኤራ፣ ሐኒኤል፣ ሪጽያ። እነዚህ ሁሉ የአሴር ዘሮች ናቸው፤ እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ ምርጥ ሰዎች፣ ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ። በትውልድ መዝገባቸው እንደ ተጻፈው ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቍጥር ሃያ ስድስት ሺሕ ነበር።