የይሳኮር ወንዶች ልጆች፤ ቶላ፣ ፉዋ፣ ያሱብ፣ ሺምሮን፤ በአጠቃላይ አራት ናቸው። የቶላ ወንዶች ልጆች፤ ኦዚ፣ ረፋያ፣ ይሪኤል፣ የሕማይ፣ ይብሣም፣ ሽሙኤል፤ እነዚህ የየቤተ ሰባቸው አለቆች ናቸው፤ በዳዊት ዘመነ መንግሥት ከቶላ ዘሮች፣ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩት የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሃያ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ነበረ። የኦዚ ወንድ ልጅ፤ ይዝረሕያ። የይዝረሕያ ወንዶች ልጆች፤ ሚካኤል፣ አብድዩ፣ ኢዩኤል፣ ይሺያ፤ ዐምስቱም አለቆች ነበሩ። ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሯቸው፣ ከቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ ሠላሳ ስድስት ሺሕ ሰዎች ነበሯቸው። ከይሳኮር ጐሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተ ሰቦቹ ትውልድ ቍጥር በአጠቃላይ ሰማንያ ሰባት ሺሕ ነበሩ።
1 ዜና መዋዕል 7 ያንብቡ
ያዳምጡ 1 ዜና መዋዕል 7
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ዜና መዋዕል 7:1-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች