1 ዜና መዋዕል 4:39-40

1 ዜና መዋዕል 4:39-40 NASV

እነርሱም ለከብቶቻቸው ግጦሽ ፍለጋ ከሸለቆው በስተምሥራቅ እስካለው እስከ ጌዶር መግቢያ ድረስ ዘልቀው ሄዱ። በዚያም ለምለምና ያማረ የግጦሽ ቦታ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊ፣ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት ነበረች። በቀድሞ ዘመን በዚህ ምድር ይኖሩ የነበሩት አንዳንድ የካም ዘሮች ናቸው።