የስምዖን ዘሮች፤ ነሙኤል፣ ያሚን፣ ያሪን፣ ዛራ፣ ሳኡል፤ ሰሎም የሳኡል ልጅ ነው፤ መብሳም የሰሎም ልጅ ነው፤ ማስማዕ ደግሞ የመብሳም ልጅ ነው። የማስማዕ ዘሮች፤ ልጁ ሃሙኤል፣ ልጁ ዛኩር፣ ልጁ ሰሜኢ። ሰሜኢ ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ ጐሣቸው በሙሉ እንደ ይሁዳ ሕዝብ ብዙ አልነበረም። የኖሩባቸውም ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ቤርሳቤህ፣ ሞላዳ፣ ሐጻርሹዓል፣ ቢልሃ፣ ዔጼም፣ ቶላድ፣ ቤቱኤል፣ ሖርማ፣ ጺቅላግ፣ ቤትማርካቦት፣ ሐጸርሱሲም፣ ቤት ቢሪ፣ ሽዓራይም፤ እስከ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ድረስ የኖሩት በእነዚህ ከተሞች ነው። በአካባቢያቸው የሚገኙት መንደሮች ደግሞ ኤጣም፣ ዓይን፣ ሬሞን፣ ቶኬን፣ ዓሻን የተባሉ ዐምስት ከተሞች ናቸው፤ በእነዚህም ከተሞች ዙሪያ እስከ ባኣል የሚዘልቁ መንደሮች ነበሩ፤ መኖሪያቸው በዚሁ ሲሆን። የትውልድ መዝገብም አላቸው። ሞሾባብ፣ የምሌክ፣ የአሜስያስ ልጅ ኢዮስያስ፣ ኢዮኤል፣ የዮሺብያ ልጅ፣ የሠራያ ልጅ፣ የዓሢኤል ልጅ ኢዩ እንዲሁም ኤልዩዔናይ፣ ያዕቆባ፣ የሾሐያ፣ ዓሣያ፣ ዓዲዔል፣ ዩሲምኤል፣ በናያስ፣ የሺፊ ልጅ ዚዛ፣ የአሎን ልጅ፣ የይዳያ ልጅ፣ የሺምሪ ልጅ፣ የሸማያ ልጅ። እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ሰዎች የየጐሣቸው መሪዎች ነበሩ። የየቤተ ሰባቸውም ብዛት እጅግ በጣም እየጨመረ ሄደ፤ እነርሱም ለከብቶቻቸው ግጦሽ ፍለጋ ከሸለቆው በስተምሥራቅ እስካለው እስከ ጌዶር መግቢያ ድረስ ዘልቀው ሄዱ። በዚያም ለምለምና ያማረ የግጦሽ ቦታ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊ፣ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት ነበረች። በቀድሞ ዘመን በዚህ ምድር ይኖሩ የነበሩት አንዳንድ የካም ዘሮች ናቸው። እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ወደዚህ ቦታ የመጡት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈጽመው አጠፏቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም፣ በዚያ መኖር ጀመሩ። ከእነዚሁ ዐምስት መቶ የሚሆኑ የስምዖን ወገኖች በይሽዒ ልጆች በፈላጥያ፣ በነዓርያ፣ በረፋያና በዑዝኤል ተመርተው የሴይርን ኰረብታማ አገር ወረሩ። አምልጠው የቀሩትን አማሌቃውያን ፈጅተው እስከ ዛሬ በዚያው ይኖራሉ።
1 ዜና መዋዕል 4 ያንብቡ
ያዳምጡ 1 ዜና መዋዕል 4
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ዜና መዋዕል 4:24-43
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች