የይሁዳ ዘሮች፤ ፋሬስ፣ ኤስሮም፣ ከርሚ፣ ሑር፣ ሦባል። የሦባል ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤት ደግሞ አሑማይንና ላሃድን ወለደ፤ እነዚህም የጾርዓውያን ጐሣዎች ናቸው። የኤጣም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይደባሽ። እኅታቸው ሃጽሌልፎኒ ትባላለች። ፋኑኤል ጌዶርን ወለደ፤ ኤጽር ደግሞ ሑሻምን ወለደ። እነዚህ የኤፍራታ የበኵር ልጅና የቤተ ልሔም አባት የሆነው የሑር ዘሮች ናቸው። የቴቁሔ አባት አሽሑር፣ ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት። ነዕራም አሑዛምን፣ ኦፌርን፣ ቴምኒን፣ አሐሽታሪን ወለደችለት፤ የነዕራ ዘሮች እነዚህ ነበሩ። የሔላ ወንዶች ልጆች፤ ዴሬት፣ ይጽሐር፣ ኤትናን ናቸው። የቆጽ ወንዶች ልጆች ዓኑብ፣ ጾቤባና፣ የሃሩም ልጅ የአሐርሔል ጐሣዎች ናቸው። ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም “በጣር የወለድሁት” ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው። ያቤጽም፣ “አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፤ እጅህ ከእኔ ጋራ ትሁን፤ ከሥቃይና ከጕዳትም ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ። እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው። የሹሐ ወንድም ክሉብ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርም ኤሽቶን ወለደ። ኤሽቶን ቤትራፋንና ፋሴሐን፣ የዒርናሐሽን ከተሞች የቈረቈረውን ተሒናን ወለደ። እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው። የቄኔዝ ወንዶች ልጆች፤ ጎቶንያል፣ ሠራያ። የጎቶንያል ወንዶች ልጆች፤ ሐታት፣ መዖኖታይ። መዖኖታይ ደግሞ ዖፍራን ወለደ። ሠራያ የኢዮአብ አባት ሲሆን፣ ኢዮአብ ጌሐራሺምን ወለደ፤ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ስለ ነበሩ ይህ ስም ተሰጣቸው። የዮፎኒ ልጅ የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ ዒሩ፣ ኤላ፣ ነዓም። የኤላ ልጅ፤ ቄኔዝ። የይሃሌልኤል ወንዶች ልጆች፤ ዚፍ፣ ዚፋ፣ ቲርያ፣ አሣርኤል። የዕዝራ ወንዶች ልጆች፤ ዬቴር፣ ሜሬድ፣ ዔፌር፣ ያሎን። ከሜሬድ ሚስቶች አንዲቱ ማርያምን፣ ሸማይንና የኤሽትሞዓን አባት ይሽባን ወለደች። አይሁዳዊት ሚስቱም የጌዶርን አባት ዮሬድን፣ የሦኮን አባት ሔቤርን፣ የዛኖዋን አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው። የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ወንዶች ልጆች፤ የገርሚው የቅዒላ አባት፣ ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ። የሺሞን ወንዶች ልጆች፤ አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሐናን፣ ቲሎን። የይሺዒ ዘሮች፤ ዞሔትና ቤንዞሔት። የይሁዳ ልጅ የሴሎም ወንዶች ልጆች፤ የሌካ አባት ዔር፣ የመሪሳና በቤት አሽቤዓ የበፍታ ጨርቅ ሠሪ የሆኑት ጐሣዎች አባት ለዓዳ፣ ዮቂም፣ የኮዜባ ሰዎች፣ ኢዮአስ፣ ሞዓብን የገዛ ሣራፍና ያሹቢሌሔም። ታሪካቸውም ጥንታዊነት ያለው ነው። ሰዎቹ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ፤ በዚያም በመቀመጥ ለንጉሡ ሸክላ ይሠሩ ነበር።
1 ዜና መዋዕል 4 ያንብቡ
ያዳምጡ 1 ዜና መዋዕል 4
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ዜና መዋዕል 4:1-23
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች