1 ዜና መዋዕል 27:23-24

1 ዜና መዋዕል 27:23-24 NASV

እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚያበዛቸው ተስፋ ሰጥቶ ስለ ነበር፣ ዳዊት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በታች የሆነውን አልቈጠረም ነበር። የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቍጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈጸመውም፤ መቈጠራቸው በእስራኤል ላይ ቍጣ ስላመጣ፣ የተቈጠረውም በንጉሡ ዳዊት መዝገብ አልገባም።