እግዚአብሔር ለዳዊት በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት፣ የሳኦልን መንግሥት አንሥተው ለርሱ ለመስጠት ዳዊት ወደሚገኝበት ወደ ኬብሮን የመጡት ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ ጋሻና ጦር አንግበው ለጦርነት የተዘጋጁት የይሁዳ ሰዎች ስድስት ሺሕ ስምንት መቶ፤ ከስምዖን ነገድ ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ሰባት ሺሕ አንድ መቶ። ከሌዊ ነገድ አራት ሺሕ ስድስት መቶ፤ የአሮን ቤተ ሰብ መሪ የሆነውን ዮዳሄን ጨምሮ ሦስት ሺሕ ሰባት መቶ ሰዎች፤ ወጣቱ ብርቱ ተዋጊ ሳዶቅና ከቤተ ሰቡ ሃያ ሁለት የጦር አለቆች፤ የሳኦል ሥጋ ዘመድ የሆኑ የብንያም ሰዎች ሦስት ሺሕ፤ ከእነዚህም አብዛኞቹ እስከዚያች ጊዜ ድረስ ለሳኦል ቤት ታማኝ ነበሩ፤ ከኤፍሬም ሰዎች በጐሣዎቻቸው ዘንድ ታዋቂ የሆኑ ብርቱ ተዋጊዎች ሃያ ሺሕ ስምንት መቶ፤ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ሰዎች፤ እነርሱም ዳዊትን ለማንገሥ በየስማቸው ተጽፈው የመጡ ነበሩ። ዘመኑን የተረዱና እስራኤላውያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ የይሳኮር ሰዎች ሁለት መቶ አለቆች፤ በእነርሱም ሥር ሆነው የሚታዘዙ ዘመዶቻቸው። ልምድ ያላቸው፣ በሁሉም ዐይነት መሣሪያ ለመዋጋት የተዘጋጁና ዳዊትን ለመርዳት የመጡት መንታ ልብ የሌላቸው የዛብሎን ሰዎች ኀምሳ ሺሕ፤ ከንፍታሌም ሰዎች አንድ ሺሕ የጦር አለቆች፤ ከእነርሱም ጋራ ጋሻና ጦር የያዙ ሠላሳ ሰባት ሺሕ ሰዎች፤ ከዳን ሰዎች ለጦርነት የተዘጋጁ ሃያ ስምንት ሺሕ ስድስት መቶ፤ ከአሴር ሰዎች ልምድ ያላቸውና ለጦርነት የተዘጋጁ ወታደሮች አርባ ሺሕ፤ ከምሥራቅ ዮርዳኖስ ከሮቤል፣ ከጋድና ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ልዩ ልዩ ዐይነት መሣሪያ የታጠቁ አንድ መቶ ሃያ ሺሕ ሰዎች። እነዚህ ሁሉ በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል ፈቃደኞች የሆኑ ተዋጊዎች ናቸው።
1 ዜና መዋዕል 12 ያንብቡ
ያዳምጡ 1 ዜና መዋዕል 12
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ዜና መዋዕል 12:23-38
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች