1
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 4:2
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ኤልሳዕም፥ “አደርግልሽ ዘንድ ምን ትሻለሽ? በቤትሽም ያለውን ንገሪኝ” አላት። እርስዋም፥ “ለእኔ ለአገልጋይህ ከዘይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አንዳች የለኝም” አለችው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 4:1
ከነቢያትም ልጆች የአንዱ ሚስት የሆነች አንዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል” ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
3
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 4:3
እርሱም፥ “ሂጂና ከጎረቤቶችሽ ሁሉ ከውጭ ባዶ ማድጋዎችን ተዋሺ፤ አታሳንሻቸውም።
4
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 4:4
ወደ ቤትሽም ገብተሽ ከአንቺና ከልጆችሽ በኋላ በሩን ዝጊ፤ ወደ እነዚህም ማድጋዎች ሁሉ ዘይቱን ገልብጪ፤ የሞላውንም ፈቀቅ አድርጊ” አላት።
5
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 4:6
ከዚህም በኋላ ልጆችዋን፥ “ደግሞ ማድጋ አምጡልኝ” አለቻቸው፤ እነርሱም፥ “ሌላ ማድጋ የለም” አሏት፤ ዘይቱም ቆመ።
6
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 4:7
መጥታም ለእግዚአብሔር ሰው ነገረችው፤ እርሱም፥ “ሄደሽ ዘይቱን ሽጭ ዕዳሽንም ክፈዪ፤ በተረፈውም ዘይት የአንቺንና የልጆችሽን ሰውነት አድኚ” አላት።
7
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 4:5
እንዲሁም ከእርሱ ሄዳ፥ በሩን ከእርስዋና ከልጆችዋ በኋላ ዘጋች፤ እነርሱም ማድጋዎቹን ወደ እርስዋ ያቀርቡላት ነበር፤ እርስዋም ትገለብጥ ነበር።
8
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 4:34
መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ አፉንም በአፉ፥ ዐይኖቹንም በዐይኖቹ፥ እጆቹንም በእጆቹ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ሰውነት ሞቀ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች