2 ነገሥት 4:34
2 ነገሥት 4:34 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ አፉንም በአፉ፥ ዐይኖቹንም በዐይኖቹ፥ እጆቹንም በእጆቹ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ሰውነት ሞቀ።
2 ነገሥት 4:34 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በዐልጋው ላይ ወጥቶም በልጁ ላይ ተጋደመና አፉን በአፉ፣ ዐይኑን በዐይኑ፣ እጁን በእጁ ላይ አደረገ። ሙሉ በሙሉ እንደተዘረጋበትም፣ የልጁ ሰውነት መሞቅ ጀመረ።
2 ነገሥት 4:34 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ አፉንም በአፉ፥ ዐይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ።