1
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:13-14
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ወንድሞች ሆይ! እኔ ግን ይህንን ነገር የራሴ አድርጌዋለሁ ብዬ አላስብም፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ ወደ ፊት እዘረጋለሁ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ያለውን የመጠራት ሽልማት እንዳገኝ ወደ ግቡ እሮጣለሁ።
對照
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:13-14 探索
2
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:10-11
በሞቱም እርሱን በመምሰል ክርስቶስንና የትንሣኤውን ኃይል መከራውንም ተካፋይ መሆኔን ማወቅ እፈልጋለሁ፤ ምናልባትም ቢሆንልኝ የሙታን ትንሣኤን እቀዳጃለሁ።
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:10-11 探索
3
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:8
አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ ለማወቅ ስል ሁሉ ነገር ጉዳት እንደሆነ አድርጌ እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ነገሮች በማጣት ተጐዳሁ፤ እነርሱንም እንደ ጉድፍ አድርጌ ቈጠርኋቸው፤ በዚህም ክርስቶስን እንዳገኝ፥
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:8 探索
4
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:7
ነገር ግን ለእኔ ጥቅም የሚያስገኘውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቈጥሬዋለሁ።
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:7 探索
主頁
聖經
計劃
影片