1
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:13
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ማንም ሰው በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ ይቅር በሉ፤
對照
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:13 探索
2
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:2
በላይ በሰማይ ስላለው አስቡ እንጂ በምድር ስላለው አታስቡ።
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:2 探索
3
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:23
ሥራችሁንም ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት እንዲሁ በትጋት ፈጽሙት፤
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:23 探索
4
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:12
እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳንና የተወደዳችሁ ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትሕትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:12 探索
5
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:16-17
የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:16-17 探索
6
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:14
በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት።
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:14 探索
7
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:1
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ፤
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:1 探索
8
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:15
በአንድ አካል ሥር ሆናችሁ የተጠራችሁበት የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ውስጥ ገዢ ይሁን፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:15 探索
9
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:5
እንግዲህ በእናንተ ያሉትን ምድራዊ ነገሮች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም፦ “ዝሙትና ርኩሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣዖትንም ማምለክ የሆነ ስግብግብነት” ናቸው፤
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:5 探索
10
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:3
ሞታችኋልና፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ውስጥ ተሰውሮአልና፤
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:3 探索
11
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:8
አሁን ግን እናንተ ቁጣንና ንዴትን ክፋትንም፥ ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ፤
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:8 探索
12
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:9-10
አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁ አስወግዳችሁታልና እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ፤ እንደ ፈጣሪውም መልክ በእውቀት የታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል፤
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:9-10 探索
13
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:19
ባሎች ሆይ! ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ የምታማርሯቸውም አትሁኑ።
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:19 探索
14
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:20
ልጆች ሆይ! ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:20 探索
15
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:18
ሚስቶች ሆይ! በጌታ ዘንድ ተገቢ ስለ ሆነ ለባሎቻችሁ ተገዙ።
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 3:18 探索
主頁
聖經
計劃
影片