የዘላለም ሕይወት预览

የዘላለም ሕይወት

9天中的第1天

እውነተኛ ሕይወት የሚገኘው ከኢየሱስ ነው።

ጌታ ኢየሱስ ስለአገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። "በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና" (ዮሐንስ 3:16)።

ጌታ ኢየሱስ ሊሰጠን የሚፈልገው ሕይወት ዘላለማዊ ነው። አንዳንድ ሰዎች እንደሚገምቱት ክርስትና የአምልኮ ሥርዓቶችና ሕጎችን የመፈጸም ግዴታና፣ ደስታ የሌለበት አሰልቺ ሕይወት አይደለም። ጌታ ኢየሱስ በአምላክ ፊት ለእኛና ላመኑት ሁሉ ሙሉ ደስታ ያለበት የዘላለም ሕይወት አቅርቦልናል። ''የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍስሐ አለ'' (መዝሙር 16:11)።

የራሱን ሕይወት በመስጠት ጌታ ኢየሱስ ይህን ዘላለማዊና የተባረከ ሕይወት ሰጥቶናል። በዮሐንስ 10፡15 ላይ እንደተጻፈው፣ ''ይህም አብ እኔን እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው ነው። ሕይወቴንም ስለ በጎቼ አሳልፌ እሰጣለሁ።'' ይህም የመጨረሻው የፍቅር ተግባር ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ሰው ለመሆን እና ነፍሱን ለኃጢአተኞች አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ ነበር። ይህንንም ያደረገው በራሱ ፈቃደኝነት ነው (ዮሐንስ 10፡ ይመልከቱ)። ኢየሱስ ሞትን በሞቱ በማሸነፍ በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖራቸው አድርጓል።

ጌታ ኢየሱስ የሚሰጠውን ይህን ሕይወት ይፈልጋሉ?

读经计划介绍

የዘላለም ሕይወት

ጌታ ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16)። ይህ የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ምን እንደሚል እንመልከት።

More