Haggai: ቀጣዩ ምን ይሆን?预览

Haggai: ቀጣዩ ምን ይሆን?

5天中的第4天

እግዚአብሔር ታዲያ ምን ይፈልጋል

በህይወትህ በሆነ ደረጃ የማይታለፍ ሆኖ የተሰማህን ግብ አሳክተህ ይሆናል፤ ለምሳሌ ልክ እንደ አካል ብቃት ወይም የክብደት መቀነስ ዕቅድ፤ ብቁ እንዳልሆንክ የተሰማህን ስራ ወይም ደግሞ ልትኖርበት የማትችለው መስሎህ የፈራኸው አለም አቀፍ ወረርሽኝ ዓይነት በሽታ። ምናልባት ውጥን የያዝክለትን ግብ ለመምታት እየወሰድክ እንዳለው የየዕለት እርምጃ ዓይነት፤ በርግጥ እንደሚቻልና አንደሚደረስበት እንዲሁም የሆነ ጊዜ ላይ አስፈሪ ሸክም የነበረው ነገር የታላቅ ደስት ምክንያት መሆኑን አስተውለሃል፡፡ ቅድስናን መከታተል ከአቅምህ በላይ እንደሆነ አድርገህ ሊሰማህ ይችላል፤ ነገር ግን ስትፀናና ለውጥ ስታመጣ ሸክሙ በእውነት በረከት መሆኑን ትገነዘባለህ። ሸክሙንም አንተ ራስህ እንዳልተሸከምከውም ልብ ትላለህ፡፡

በሐጌ በኩል እግዚአብሔር ያለማቋረጥ ህዝቡን ከእርሱ ጋር ወዳለው ህብረት ሲስብ ተመልክተናል። በዚህም እንዴት ጥርት ባለ ሁኔታ እንደ እርሱ ቅዱስ የሆነን ኑሮ እንዲኖሩ ሲጠራቸው አይተናል፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ እውነት ለመናገር የእግዚአብሔር ቅድስና ለሰው እጅግ አስፈሪ ነው፡፡ በእርሱ ፍፅምና፣ በሁሉ ቦታ መገኘት እና ሁሉን አዋቂነት ምክንያት የእኛ አለመቀደስ ግን ትኩረት ያላገኘና የማይፈታ ሊሆን አይችልም፡፡ እግዚአብሔር ወደ እርሱ ይስበናል፤ ነገር ግን ወደ ህልውናው እየተጠጋን ስንመጣ እኛም እንደ እርሱ ቅዱስ እንሆናል፡፡ ይህ እኛ የምንሸከመው ትልቅ ሸክም ሊመስለን ይችላል ነገር ግን ደስ የሚያሰኝ በረከት ሊሆንም ይችላል፤ ምክንያቱም እኛ ቅድስናን የምንከታተለው በእግዚአብሔር ብርታት እንጂ በእኛ አይደለም፡፡

ሐጌ ቅድስና ሊተላለፍ እንደማይችል ይገልፃል፤ ቅድስና ማጣት ግን ተላላፊ ነው። የእግዚአብሔር ህዝብ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በመቆየት ብቻ ቅዱስ ለመሆን ተስፋ ሲያደርጉ ነበር፤ ልባቸው ግን በትክክለኛው ቦታ አልነበረም፤ አሁንም በዙሪያቸው ያለውን ባህል ርኩሰት ተከተሉ። አንድ ነገር ካልነፃ ወይም ቅዱስ ካልሆን ብልሽት ይገጥማል (ልክ እንደ እኛ)፣ መልሶም ርኩስ ያደርገዋል፣ ይህንን ልውውጥ ለመስበር አንድ ቅዱስ የሆነ ያስፈልጋል እርሱም እግዚአብሔር! እግዚአብሔር የሚያስፈልገን ቅድስና ያለው ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ልባችንን በመቀየርና አእምሮአችንን በማደስ ቅድስናውን እንድንቀበል ማድረግ የሚችልም ነው፡፡

ስለዚህ ከቅድስና አንጻር እግዚአብሔር እኛን የሚፈልገው እርሱ ምንጭም ሰጪም በመሆኑ ነው። የቤተ መቅደሱ እንደገና መገንባት ተጨባጭ የእግዚአብሔርን ህዝብ የተለወጠ ልብ መገለጫ ነው፡፡ በመጀመሪያው ጅምር የመታዘዝ እርምጃቸው አግኝቷቸው ስለ ተትረፈረፈው የህልውናው በረከት ተስፋ ሰጣቸው፡፡

እኛ እንደ እርሱ ቅዱሳን እንሆን ዘንድ ኢየሱስ በሞቱ የዓለምን ርኩሰት በራሱ ላይ አኖረ። ህያው የሆነው መቅደሳችን እንደገና ተገንብቷልና ኢየሱስ ከሞት የተነሳበትን ቀን እናክብር፡፡ በምንናገረው፣ በምናየውና በምንፈልገው ሁሉ ቅድስናን እየተከተልን እርስ በርሳችን እንበረታታ፡፡

读经计划介绍

Haggai: ቀጣዩ ምን ይሆን?

ነገህን እየፈራህ ከሆነ ይህ የአምስት ቀናት እቅድ ለአንተ ነው፡፡ ምናልባት ልትቋቋመው የማትችለው አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞህ ይሆናል፤ ነገር ግን በአንድ ነገር እርግጠኛ ሆነህ ኑር ይኸውም በአንተ ሕይወት የመጨረሻው ቃል ያለው እግዚአብሔር ነው፡፡ አግዚአብሐርን ማስቀደም፣ ህወትህን ከዓላማው ጋር ማጣጣም፤ በሚያጠነክርህና ቀጣዩ ምን እንደሆነ በሚያስቀጥልህ እውነት ላይ ማረፍን ተማር፡፡

More