BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች预览

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

28天中的第17天

የእግዚአብሔር መንገዶች እውነተኛ ደስታንና ጥበብ ለሰው ልጆች ይሰጣሉ (መዝሙር 19÷7-8ን ይመልከቱ)። ሰይጣን ግን ሰዎች የራሳቸውን መንገድ ጥበብ የሞላበት አድርገው እንዲቆጥሩ ይፈልጋል (ዘፍጥረት 3÷6ን ይመልከቱ)። የሰይጣን ሽንገላዎች በጊዚያዊ ደስታ ታጅበው ስለሚመጡ በነሱ መታለል ቀላል ነው። ሰዎች በእግዚአብሔር ትዕዛዞች ፈንታ የራሳቸው የሆነውን ሲመርጡ፣ የሚፈልጉትን እውነተኛና ዘላቂ ደስታ ማግኘት አይችሉም።

ያንብቡ፦

መዝሙር 19÷7-11፣ ዘፍጥረት 3÷1-7

ምልከታዎን ያስፍሩ፡

የዛሬውን ሁለት ምንባቦች ያነጻጽሩ። በሁለቱም ምንባቦች ውስጥ የትኞቹ ቃላትና ጽንሰ-ሐሳቦች ተደጋግመዋል? ምን ያስተውላሉ?

እግዚአብሔር በእርስዎ ላይ ያለው አላማ በጎ ስለመሆኑ እምነትዎ እንዲታደስ ይጸልዩ። ከእርሱ ጋር ስላልተስማሙበት ነገር ወይም እርሱን ስለተጠራጠሩት ነገር ታማኝ ሁነው ይንገሩት፤ ዛሬ የእርሱን ምሪት ለመከተል የሚያስፈልግዎን ነገርም ይጠይቁት።

读经计划介绍

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።

More