እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥ预览

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥ

6天中的第3天

መስቀሉን እንደገና መተርጎም

ክስተቶች ተቃራኒ የሆነ መልዕክት ይዘው የሚናገሩ በሚመስሉበት ጊዜ ውስጥ የድልን እና የትንሳኤን ምስክርነት የመያዝን ፈተና ይዘናል። ነገር ግን በእውነተኛው ትንሣኤ ወቅት ለደቀመዛሙርቱ የተለየ ሁኔታ እንዳልነበር በማሰብ መፅናናት እንችላለን፡፡ ከላይ ባለው ምንባብ በደቀመዛሙርቱ ልብ ውስጥ ያለውን ግራ መጋባት እናያለን፡፡ ስለ ኢየሱስ ትንሣኤ የሚናገሩ የተለያዩ ሪፖርቶችን ይሰማሉ፣ እናም ለማመን አጥብቀው ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን በሁለቱ ምስክርነቶች መካከል ተወጥረዋል፣  “በተከናወኑት ነገሮች” (ቁ 18) ምስክርነት እና የትንሣኤው ምስክርነቶች፡፡ ኢየሱስ በዚህ ሰዓት ነው በውይይቱ ላይ የገባው፡፡

ይገርማል! በችግራችን ውስጥ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ለመግለጥ የማይፈራ በመሆኑ ምስጋና ይገባዋል፤ በአለማመናችን መካከል ወደ እኛ የሚወርድ መሐሪ ነው!

በቁጥር ሃያ አንድ ላይ ደቀመዛሙርቱ ምን እንዳሉ ልብ ይበሉ “ተስፋ ያደረግነው እርሱ ነበር” (ያለፈን ነገር የሚያሳይ ሐረግ)! የተከናወኑት ነገሮች (ስቅለቱ) የደቀ መዛሙርቱን እምነት ወደ ድንጋጤ ቀየረው፡፡ ደቀመዛሙርቱ ሁሉንም ነገር (ኢየሱስንም ራሱ) በተከናወነው ነገር ዕይታ እየረጎሙ ነበር፡፡ ይህ ነው የኢየሱስን መልስ የበለጠ ኃያል ያደረገው!

ኢየሱስ ራሱን መግለጡ ብቻ ሳይሆን ራሱን የገለጠበት መንገድ ነው፡፡ የደቀ መዛሙርቱ ዓይኖች መከፈት መገለጡ የጀመረበት ቦታ አይደለም፡፡ እርሱ በቅዱስ መጽሃፍት ጀመረ! በቅዱሳት መጻሕፍት አማካይነት የተከናወኑትን  ክስተቶች ኢየሱስ ያስረዳቸው ጀመረ! ይህንንም ሲያደርግ ደቀመዛሙርቱ በኋላ ኢየሱስ ሲያነጋግራቸው ልባቸው እንዴት ይቃጠል እንደነበር መሰከሩ፡፡

ከቅዱሳት መጻሕፍት መጀመር አለብን! በዙሪያችን እየተከሰቱ ያሉትን ነገሮች የመተርጎም ኃይል ከመስጠት ይልቅ ቅዱሳት መጻሕፍት በዙሪያችን ያሉትን ክስተቶች እንዲተረጉሙ ፍቀዱላቸው! ይህን ስናደርግ፣ ግራ መጋባትና በፍርሃት ከመዋጥ ይልቅ ልባችን በተስፋ እና በእምነት እንደሚቃጠል አምናለሁ!

የሕይወት ተዛምዶ
ቀንዎን በቅዱሳት መጻህፍት በመጀመር በሕይወትዎ ውስጥ ለእግዚአብሔር ቃል ቅድሚያ ይስጡ እና እግዚአብሔር በቃሉ በኩል ራሱን እንዲገልጥ እመኑት፡፡

ፀሎት
ጌታ ሆይ፣ ዓይኖቼን ወደ ቃልህ ክፈት፡፡ በቃልህ ብርሃን በዙሪያዬ የሚከናወኑትን ክስተቶች እንዳይ እርዳኝ፡፡ ልቤም በምስክርነቱ ቃል ይቃጠል!

读经计划介绍

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥ

በዚህ የ6 ቀን ጥናት ውስጥ ፍርሃት፣ ግራ መጋባትና ጭንቀትን ለማስወገድ በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔር መኖር ምን ያህል ማድረግ እንደሚችል እናያለን። ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ በማሳለፍና ከቃሉ በመማር እነዚህን ተግዳሮቶች እንዴት ማሸነፍ እንደምንችል፣ ትኩረታችንን እንዴት እንደምናስተካክልና አስተሳሰባችንን እንደምንለውጥ እናያለን።

More