1
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:58
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።
对照
探索 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:58
2
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:57
ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ድልን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
探索 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:57
3
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:33
አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”
探索 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:33
4
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:10
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ ይልቁን ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ሆኖም ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።
探索 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:10
5
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:55-56
“ሞት ሆይ፤ ድል መንሣትህ የት አለ? ሞት ሆይ፤ መውጊያህስ የት አለ?”። የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው፤ የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው።
探索 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:55-56
6
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:51-52
እነሆ፥ አንድ ምስጢር እነግራችኋለሁ! ሁላችን አናንቀላፋም፤ ነገር ግን ሁላችንም እንለወጣለን፤ የመጨረሻው መለከት ሲነፋ፥ ድንገት፥ በቅጽበተ ዐይን፥ መለከት ይነፋል፤ ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን።
探索 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:51-52
7
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:21-22
ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደመጣ፥ የሙታንም ትንሣኤ በአንድ ሰው በኩል ሆኖአልና። ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፥ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤
探索 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:21-22
8
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:53
የሚጠፋው የማይጠፋውን፥ የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።
探索 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:53
9
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:25-26
ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ ሥር እስከሚያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና። የሚደመሰሰው የመጨረሻው ጠላት ሞት ነው፤
探索 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:25-26
主页
圣经
计划
视频