YouVersion 标志
圣经计划视频
获取软件
选择语言
搜索图标

ኦሪት ዘፍጥረት 1 的热门经文

1

ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ሰውን በመልካችንና በአምሳያችን እንፍጠር፤ ሰዎችም በባሕር ውስጥ በሚኖሩ ዓሣዎች፥ በሰማይ በሚበርሩ ወፎች፥ በእንስሶችና በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ በሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች፥ እንዲሁም በምድር ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ። በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎም ፈጠራቸው።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27

2

ኦሪት ዘፍጥረት 1:28

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

እግዚአብሔርም “ብዙ፤ ተባዙ፤ ዘራችሁ ምድርን ይሙላ፤ ምድርም በቊጥጥራችሁ ሥር ትሁን፤ በባሕር ውስጥ በሚኖሩ ዓሣዎች፥ በሰማይ በሚበርሩ ወፎችና በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራችሁ” ብሎ ባረካቸው።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:28

3

ኦሪት ዘፍጥረት 1:1

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:1

4

ኦሪት ዘፍጥረት 1:2

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

በዚያን ጊዜ ምድር ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍ ነበር።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:2

5

ኦሪት ዘፍጥረት 1:3

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:3

6

ኦሪት ዘፍጥረት 1:31

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

እግዚአብሔር የፈጠረውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፥ እጅግ መልካም ነበረ። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱ ነጋ፤ ስድስተኛ ቀን ሆነ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:31

7

ኦሪት ዘፍጥረት 1:4

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

እግዚአብሔርም፥ ብርሃን መልካም መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔርም ብርሃንን ከጨለማ ለየ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:4

8

ኦሪት ዘፍጥረት 1:29

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ምግብ እንዲሆኑአችሁ በምድር ገጽ ላይ የሚገኙትን የእህል አዝርዕትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን ሁሉ ሰጥቻችኋለሁ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:29

9

ኦሪት ዘፍጥረት 1:5

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

እግዚአብሔር ብርሃኑን “ቀን” ብሎ ጠራው፤ ጨለማውንም “ሌሊት” ብሎ ሰየመው። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ ይህም አንድ ቀን ሆነ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:5

10

ኦሪት ዘፍጥረት 1:6

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ውሃውን ከውሃ የሚለይ ጠፈር ይሁን” አለ፤

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:6

11

ኦሪት ዘፍጥረት 1:30

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

እንዲሁም በምድር ላይ ለሚኖሩ እንስሶች ሁሉ፥ በሰማይ ለሚበርሩ ወፎች ሁሉ፥ በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ ለሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ፥ በአጠቃላይ የሕይወት እስትንፋስ ላለው ፍጥረት ሁሉ ምግብ እንዲሆናቸው ልምላሜ ያለውን ሣርና ቅጠል ሁሉ ሰጥቻቸዋለሁ።” እንዲሁም ሆነ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:30

12

ኦሪት ዘፍጥረት 1:14

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ቀንን ከሌሊት ለመለየት ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ ይሁኑ፤ ለዕለታት፥ ለክፍላተ ዓመትና ለዓመታት መለያ ምልክት ይሁኑ፤

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:14

13

ኦሪት ዘፍጥረት 1:11

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር አትክልትን፥ የእህል አዝርዕትን፥ ፍሬ የሚያፈሩ የፍሬ ዛፎችንና ተክሎችን በየዐይነቱ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:11

14

ኦሪት ዘፍጥረት 1:7

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ጠፈርን ፈጠረ፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር “ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉት ውሆች ይለያዩ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:7

15

ኦሪት ዘፍጥረት 1:12

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

በዚህ ዐይነት ምድር አትክልትን፥ በየዐይነቱ የእህል አዝርዕትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን አበቀለች፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:12

16

ኦሪት ዘፍጥረት 1:16

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን ፈጠረ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን፥ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲያበሩ አደረገ፤ እንዲሁም ከዋክብትን ፈጠረ፤

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:16

17

ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “የብሱ ግልጥ ሆኖ እንዲታይ ከሰማይ በታች ያለው ውሃ ሁሉ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” ብሎ ሰየመው፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10

18

ኦሪት ዘፍጥረት 1:22

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

እግዚአብሔር “ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ የባሕርን ውሃ ይሙላ፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:22

19

ኦሪት ዘፍጥረት 1:24

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር ሕይወት ያላቸው ፍጥረቶችን፥ እንደየዐይነታቸው እንስሶችን፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችንና አራዊትን እንደየዐይነታቸው ታስገኝ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:24

20

ኦሪት ዘፍጥረት 1:20

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ውሃ ሕይወት ባላቸው በልዩ ልዩ ፍጥረቶች የተሞላ ይሁን፤ ወፎችም ከምድር በላይ ባለው በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:20

21

ኦሪት ዘፍጥረት 1:25

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር የምድር አራዊትን በየዐይነቱ፥ እንስሶችን በየዐይነታቸው በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችን በየዐይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 1:25

上一章
下一章
YouVersion

我们要鼓励、挑战你每天亲近上帝。

事工

关于我们

就职机会

义工

博客

新闻区

有用链接

帮助

捐赠

圣经译本

音频圣经

译本语言

今日经文


此数字事工属于

Life.Church
English (US)

©2025 Life.Church / YouVersion

隐私政策使用条款
漏洞披露方案
FacebookTwitterInstagramYouTubePinterest

主页

圣经

计划

视频