1
ወደ ሮም ሰዎች 12:2
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:2
2
ወደ ሮም ሰዎች 12:1
እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:1
3
ወደ ሮም ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:12
4
ወደ ሮም ሰዎች 12:21
ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:21
5
ወደ ሮም ሰዎች 12:10
በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:10
6
ወደ ሮም ሰዎች 12:9
ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:9
7
ወደ ሮም ሰዎች 12:18
ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:18
8
ወደ ሮም ሰዎች 12:19
ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:19
9
ወደ ሮም ሰዎች 12:11
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:11
10
ወደ ሮም ሰዎች 12:3
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:3
11
ወደ ሮም ሰዎች 12:17
ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:17
12
ወደ ሮም ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:16
13
ወደ ሮም ሰዎች 12:20
ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:20
14
ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
15
ወደ ሮም ሰዎች 12:13
ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:13
16
ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò