1
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ይህን ዓለም አትምሰሉ፤ ልባችሁንም አድሱ፤ እግዚአብሔር የሚወደውን መልካሙንና እውነቱን፥ ፍጹሙንም መርምሩ።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1
ወንድሞቻችን፥ ሰውነታችሁን ለእግዚአብሔር ሕያውና ቅዱስ፥ ደስ የሚያሰኝም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እማልዳችኋለሁ። ይህም በዕውቀት የሚሆን አገልግሎታችሁ ነው።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ ለጸሎት ትጉ።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:12
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:21
ክፉውን በመልካም ሥራ ድል ንሣው እንጂ ክፉውን በክፉ ድል አትንሣው።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:21
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:10
እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት መዋደድ ተዋደዱ፤ የምትራሩም ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ መምህሮቻችሁንም አክብሩ።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:10
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:9
ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን፤ ከክፉ ራቁ፤ በጎውንም ያዙ፤ ለጽድቅ አድሉ፤
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:9
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:18
ቢቻላችሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:18
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:19
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:19
9
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:11
ለሥራ ከመትጋት አትስነፉ፤ በመንፈስ ሕያዋን ሁኑ፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:11
10
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3
በተሰጠኝ በእግዚአብሔር ጸጋ ሁላችሁም እንዳትታበዩ እነግራችኋለሁ፤ ራሳችሁን ከዝሙት የምታነጹበትን ዐስቡ እንጂ ትዕቢትን አታስቡ፤ ሁሉም እንደ እምነቱ መጠን እግዚአብሔር እንደ አደለው ይኑር።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3
11
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:17
ክፉ ላደረገባችሁም ክፉ አትመልሱለት፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎውን ተነጋገሩ።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:17
12
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁም በአንድ ዐሳብ ተስማሙ፤ ትዕቢትን ግን አታስቡ፤ ራሱን የሚያዋርደውንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋቆች ነን አትበሉ።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16
13
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:20
ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማም አጠጣው፤ ይህን ብታደርግ የእሳት ፍሕም በራሱ ላይ ትከምራለህ።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:20
14
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚለው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሰው ጋርም አልቅሱ።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:14-15
15
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:13
በችግራቸው ቅዱሳንን ለመርዳት ተባበሩ፤ እንግዳ መቀበልንም አዘውትሩ።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:13
16
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:4-5
በአንዱ ሰውነታችን ብዙ የአካል ክፍሎች እንዳሉ፥ ሥራቸውም ልዩ ልዩ እንደ ሆነ፥ እንዲሁ ሁላችን ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፤ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው አካሎች ነን፤ ስጦታውም ልዩ ልዩ ነው፤
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 12:4-5
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò