1
የማቴዎስ ወንጌል 15:18-19
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው። ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 15:18-19
2
የማቴዎስ ወንጌል 15:11
ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፤ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው፤” አላቸው።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 15:11
3
የማቴዎስ ወንጌል 15:8-9
‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል፤’ ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።”
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 15:8-9
4
የማቴዎስ ወንጌል 15:28
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ “አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ፤” አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 15:28
5
የማቴዎስ ወንጌል 15:25-27
እርስዋ ግን መጥታ “ጌታ ሆይ! እርዳኝ፤” እያለች ሰገደችለት። እርሱ ግን መልሶ “የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም፤” አለ። እርስዋም “አዎን ጌታ ሆይ! ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ፤” አለች።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 15:25-27
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò