1
የሐዋርያት ሥራ 2:38
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ጴጥሮስም “ንስሐ ግቡ፤ ኀጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí የሐዋርያት ሥራ 2:38
2
የሐዋርያት ሥራ 2:42
በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቁረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።
Ṣàwárí የሐዋርያት ሥራ 2:42
3
የሐዋርያት ሥራ 2:4
በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፤ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።
Ṣàwárí የሐዋርያት ሥራ 2:4
4
የሐዋርያት ሥራ 2:2-4
ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፤ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፤ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።
Ṣàwárí የሐዋርያት ሥራ 2:2-4
5
የሐዋርያት ሥራ 2:46-47
በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቆረሱ፥ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር፤ እግዚአብሔርም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።
Ṣàwárí የሐዋርያት ሥራ 2:46-47
6
የሐዋርያት ሥራ 2:17
“እግዚአብሔር ይላል ‘በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤
Ṣàwárí የሐዋርያት ሥራ 2:17
7
የሐዋርያት ሥራ 2:44-45
ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤ ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር።
Ṣàwárí የሐዋርያት ሥራ 2:44-45
8
የሐዋርያት ሥራ 2:21
የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።’
Ṣàwárí የሐዋርያት ሥራ 2:21
9
የሐዋርያት ሥራ 2:20
ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።
Ṣàwárí የሐዋርያት ሥራ 2:20
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò