1
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:32
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።
Thelekisa
Phonononga ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:32
2
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:2
በትሕትናና በየዋህነት ሁሉ፥ በትዕግሥትም እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤
Phonononga ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:2
3
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:29
እንደ አስፈላጊነቱ፥ ለሚሰሙት ጸጋን እንዲሰጥ፥ ለማነጽ የሚጠቅም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።
Phonononga ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:29
4
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:31
መራርነትና ንዴት ቁጣም፥ ጩኸትና ስድብን ሁሉ፥ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።
Phonononga ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:31
5
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:26-27
ተቆጡ፥ ኃጢአትን ግን አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፤ ለዲያብሎስም ስፍራ አትስጡት።
Phonononga ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:26-27
6
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:22-24
ስለ ቀድሞ አኗኗሯችሁም፥ በሚያታልል ምኞቱ የጎደፈውንና የተበላሸውን፥ አሮጌ ሰው አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፤ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።
Phonononga ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:22-24
7
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:3
በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።
Phonononga ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:3
8
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:11-13
አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ የሰጠ እርሱ ነው፤ ይህም የክርስቶስ አካል ለመገንባት፥ ቅዱሳንን ለአገልግሎት ሥራ ለማዘጋጀት ነው፤ ይህም ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ፍጽምናው እስክንደርስ ድረስ ነው።
Phonononga ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:11-13
9
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:14-15
ከእንግዲህ እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል፥ በሰዎችም ማታለል ምክንያት፥ በነፈሰው የትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን፥ ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን፥ ሕፃናት መሆን አይገባንም። ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየተናገርን፥ በነገር ሁሉ ራስ ወደሚሆን ወደ እርሱ ወደ ክርስቶስ እንደግ፤
Phonononga ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:14-15
Ekuqaleni
IBhayibhile
Izicwangciso
Iividiyo