1
የሉቃስ ወንጌል 5:4
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ንግግሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ “ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል፤ መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ፤” አለው።
Karşılaştır
የሉቃስ ወንጌል 5:4 keşfedin
2
የሉቃስ ወንጌል 5:5-6
ስምዖንም መልሶ፦ “አቤቱ! ሌሊቱን ሙሉ ብንደክምም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ፤” አለው። ይህንም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረቦቻቸውም ተቀደዱ።
የሉቃስ ወንጌል 5:5-6 keşfedin
3
የሉቃስ ወንጌል 5:16
እርሱ ግን ገለል ብሎ ወደ በምድረ በዳዎች እየሄደ ይጸልይ ነበር።
የሉቃስ ወንጌል 5:16 keşfedin
4
የሉቃስ ወንጌል 5:32
ኀጢአተኞችን ወደ ንስሓ ልጠራ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።”
የሉቃስ ወንጌል 5:32 keşfedin
5
የሉቃስ ወንጌል 5:8
ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ፊት ወድቆ፦ “ጌታ ሆይ! እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና ከኔ ራቅ፤” አለው።
የሉቃስ ወንጌል 5:8 keşfedin
6
የሉቃስ ወንጌል 5:31
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፤
የሉቃስ ወንጌል 5:31 keşfedin
7
የሉቃስ ወንጌል 5:11
ታንኳዎቹንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።
የሉቃስ ወንጌል 5:11 keşfedin
8
የሉቃስ ወንጌል 5:12-13
ከከተማዎችም በአንዲቱ ሳለ፥ እነሆ፥ ለምጽ የወረሰው አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስንም ባየው ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ፦ “ጌታ ሆይ! ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ሲል ተማጸነው። እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ፤” አለው፤ ወዲያውም ለምጹ ለቀቀው።
የሉቃስ ወንጌል 5:12-13 keşfedin
9
የሉቃስ ወንጌል 5:15
ስለ እርሱ የሚባለው ግን ይበልጡን በስፋት ተሰራጨ፤ ብዙ ሕዝብም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ይሰበሰቡ ነበር፤
የሉቃስ ወንጌል 5:15 keşfedin
Ana Sayfa
Kutsal Kitap
Okuma Planları
Videolar