1
የዮሐንስ ወንጌል 19:30
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከቀመሰ በኋላ “ተፈጸመ!” አለ። ራሱን ዘንበል አድርጎም ነፍሱን ሰጠ።
Primerjaj
Razišči የዮሐንስ ወንጌል 19:30
2
የዮሐንስ ወንጌል 19:28
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉም ነገር እንደ ተፈጸመ ዐውቆ በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈውም ቃል እንዲፈጸም “ተጠማሁ!” አለ።
Razišči የዮሐንስ ወንጌል 19:28
3
የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
ኢየሱስ እናቱንና የሚወደውን ደቀ መዝሙር አጠገቡ ቆመው ባያቸው ጊዜ፥ እናቱን “እናቴ ሆይ! እነሆ፥ ልጅሽ!” አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን “እነኋት እናትህ!” አለው፤ ከዚያ ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።
Razišči የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
4
የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
ወደ ኢየሱስ በሄዱ ጊዜ ግን፥ እርሱ ቀደም ብሎ እንደ ሞተ አይተው፥ ጭኑን አልሰበሩም። ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ፥ ጐኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውኑ ከጐኑ ደምና ውሃ ወጣ።
Razišči የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
5
የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
ይህም የሆነው፥ “ከእርሱ አንድ አጥንት እንኳ አይሰበርም” የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። ደግሞም በሌላው የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል “ያንን የወጉትን ያዩታል” ይላል።
Razišči የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
6
የዮሐንስ ወንጌል 19:17
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ፥ “የራስ ቅል” ወደሚባለው ስፍራ ወጣ፤ ይህ ስፍራ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ጎልጎታ” ይባላል፤
Razišči የዮሐንስ ወንጌል 19:17
7
የዮሐንስ ወንጌል 19:2
ወታደሮችም የእሾኽ አክሊል ጐንጒነው በኢየሱስ ራስ ላይ አደረጉ፤ ቀይ ልብስም አለበሱት።
Razišči የዮሐንስ ወንጌል 19:2
Domov
Sveto pismo
Bralni načrti
Videoposnetki