1
ኦሪት ዘፍጥረት 17:1
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
አብራም 99 ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ ኤልሻዳይ ሁሉን የምችል አምላክ ነኝ፤ ለእኔ በመታዘዝ ዘወትር ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ፤
Primerjaj
Razišči ኦሪት ዘፍጥረት 17:1
2
ኦሪት ዘፍጥረት 17:5
የብዙ ሕዝቦች አባት ስለማደርግህም ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ አብራም መሆኑ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል።
Razišči ኦሪት ዘፍጥረት 17:5
3
ኦሪት ዘፍጥረት 17:7
“በአንተና በዘርህ፥ በመጪውም ትውልድ መካከል ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም አጸናለሁ፤ በዚህም ዐይነት ለአንተና ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
Razišči ኦሪት ዘፍጥረት 17:7
4
ኦሪት ዘፍጥረት 17:4
“ከአንተ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አደርግሃለሁ፤
Razišči ኦሪት ዘፍጥረት 17:4
5
ኦሪት ዘፍጥረት 17:19
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ትለዋለህ፤ ቃል ኪዳኔን ከእርሱና ከዘሩ ጋር ለዘለዓለም አጸናለሁ፤
Razišči ኦሪት ዘፍጥረት 17:19
6
ኦሪት ዘፍጥረት 17:8
አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን ይህችን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ መላውን የከነዓን ምድር ለዘለዓለም እንዲወርሱት ለዘርህ እሰጣለሁ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”
Razišči ኦሪት ዘፍጥረት 17:8
7
ኦሪት ዘፍጥረት 17:17
አብርሃም ግንባሩ መሬት እስኪነካ ድረስ ዝቅ ብሎ ሰገደ፤ ነገር ግን “ዕድሜው መቶ ዓመት የሆነው ሰው ልጅ መውለድ ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመትዋ ልጅ ልትወልድ ትችላለችን?” ብሎ በማሰብ ሳቀ፤
Razišči ኦሪት ዘፍጥረት 17:17
8
ኦሪት ዘፍጥረት 17:15
እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ከእንግዲህ ወዲህ ሚስትህን ሣራይ ብለህ አትጥራት፤ ከዛሬ ጀምሮ የእርስዋ ስም ሣራ ነው።
Razišči ኦሪት ዘፍጥረት 17:15
9
ኦሪት ዘፍጥረት 17:11
ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል፤
Razišči ኦሪት ዘፍጥረት 17:11
10
ኦሪት ዘፍጥረት 17:21
ነገር ግን የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ከሣራ ከሚወለደው ልጅህ ከይስሐቅ ጋር ቃል ኪዳኔን አጸናለሁ።”
Razišči ኦሪት ዘፍጥረት 17:21
11
ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13
በመጪው ዘመን የሚወለድ ወንድ ልጅ ሁሉ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ይገረዝ፤ እንዲሁም በቤትህ የተወለዱና በቤትህ ሳይወለዱ ከውጪ በገንዘብ ተገዝተው የመጡ ባሪያዎች ሳይቀሩ በዚሁ ዐይነት ይገረዙ። ቃል ኪዳኔ ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር የሚኖር መሆኑን የሚያሳይ የሥጋ ምልክት እንዲሆን እያንዳንዱ ወንድ ይገረዝ።
Razišči ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13
Domov
Sveto pismo
Bralni načrti
Videoposnetki