1
የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
መብራትን አብርተው በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል እንጂ ከዕንቅብ በታች አያኖሩትም፤ በቤትም ላሉት ሁሉ ያበራል። መልካም ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ እንግዲህ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ።
Compară
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16
2
የማቴዎስ ወንጌል 5:14
እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:14
3
የማቴዎስ ወንጌል 5:8
ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:8
4
የማቴዎስ ወንጌል 5:6
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ይጠግባሉና።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:6
5
የማቴዎስ ወንጌል 5:44
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:44
6
የማቴዎስ ወንጌል 5:3
በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:3
7
የማቴዎስ ወንጌል 5:9
ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:9
8
የማቴዎስ ወንጌል 5:4
የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መፅናናትን ያገኛሉና።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:4
9
የማቴዎስ ወንጌል 5:10
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:10
10
የማቴዎስ ወንጌል 5:7
ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:7
11
የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12
“ሲሰድቡአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12
12
የማቴዎስ ወንጌል 5:5
የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:5
13
የማቴዎስ ወንጌል 5:13
እናንተ የምድሪቱ ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ቢያጣ ግን በምን ይጣፍጣል? በሰው ለመረገጥ ወደ ውጭ ከመጣል በስተቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:13
14
የማቴዎስ ወንጌል 5:48
ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:48
15
የማቴዎስ ወንጌል 5:37
ስለዚህ ንግግራችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከእነዚህ የተረፈ ግን ከክፉው ነው።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:37
16
የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39
“‘ዐይን ስለ ዐይን፥ ጥርስ ስለ ጥርስ’ እንደተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ክፉውን አትቃወሙት፤ ነገር ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39
17
የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30
ቀኝ ዐይንህ ብታሰናክልህ ከአንተ አውጥተህ ጣላት፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከሰውነትህ አንዱ ክፍል ቢጠፋ ይሻልሃልና። ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ከአንተ ቆርጠህ ጣላት፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከሰውነትህ አንዱ ክፍል ቢጠፋ ይሻልሃልና።
Explorează የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30
Acasă
Biblia
Planuri
Videoclipuri