1
ኦሪት ዘፍጥረት 17:1
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
አብራም 99 ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ ኤልሻዳይ ሁሉን የምችል አምላክ ነኝ፤ ለእኔ በመታዘዝ ዘወትር ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ፤
Compare
ኦሪት ዘፍጥረት 17:1ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
ኦሪት ዘፍጥረት 17:5
የብዙ ሕዝቦች አባት ስለማደርግህም ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ አብራም መሆኑ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል።
ኦሪት ዘፍጥረት 17:5ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
ኦሪት ዘፍጥረት 17:7
“በአንተና በዘርህ፥ በመጪውም ትውልድ መካከል ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም አጸናለሁ፤ በዚህም ዐይነት ለአንተና ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
ኦሪት ዘፍጥረት 17:7ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
ኦሪት ዘፍጥረት 17:4
“ከአንተ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አደርግሃለሁ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 17:4ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
ኦሪት ዘፍጥረት 17:19
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ትለዋለህ፤ ቃል ኪዳኔን ከእርሱና ከዘሩ ጋር ለዘለዓለም አጸናለሁ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 17:19ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
ኦሪት ዘፍጥረት 17:8
አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን ይህችን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ መላውን የከነዓን ምድር ለዘለዓለም እንዲወርሱት ለዘርህ እሰጣለሁ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 17:8ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
ኦሪት ዘፍጥረት 17:17
አብርሃም ግንባሩ መሬት እስኪነካ ድረስ ዝቅ ብሎ ሰገደ፤ ነገር ግን “ዕድሜው መቶ ዓመት የሆነው ሰው ልጅ መውለድ ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመትዋ ልጅ ልትወልድ ትችላለችን?” ብሎ በማሰብ ሳቀ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 17:17ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
ኦሪት ዘፍጥረት 17:15
እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ከእንግዲህ ወዲህ ሚስትህን ሣራይ ብለህ አትጥራት፤ ከዛሬ ጀምሮ የእርስዋ ስም ሣራ ነው።
ኦሪት ዘፍጥረት 17:15ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
ኦሪት ዘፍጥረት 17:11
ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል፤
ኦሪት ዘፍጥረት 17:11ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
10
ኦሪት ዘፍጥረት 17:21
ነገር ግን የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ከሣራ ከሚወለደው ልጅህ ከይስሐቅ ጋር ቃል ኪዳኔን አጸናለሁ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 17:21ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
11
ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13
በመጪው ዘመን የሚወለድ ወንድ ልጅ ሁሉ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ይገረዝ፤ እንዲሁም በቤትህ የተወለዱና በቤትህ ሳይወለዱ ከውጪ በገንዘብ ተገዝተው የመጡ ባሪያዎች ሳይቀሩ በዚሁ ዐይነት ይገረዙ። ቃል ኪዳኔ ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር የሚኖር መሆኑን የሚያሳይ የሥጋ ምልክት እንዲሆን እያንዳንዱ ወንድ ይገረዝ።
ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ