1
ወደ ሮም ሰዎች 3:23-24
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
နှိုင်းယှဉ်
ወደ ሮም ሰዎች 3:23-24ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
ወደ ሮም ሰዎች 3:22
እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤
ወደ ሮም ሰዎች 3:22ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
ወደ ሮም ሰዎች 3:25-26
እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው።
ወደ ሮም ሰዎች 3:25-26ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
ወደ ሮም ሰዎች 3:20
ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና።
ወደ ሮም ሰዎች 3:20ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
ወደ ሮም ሰዎች 3:10-12
እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ ቸርነት የሚያደርግ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም።
ወደ ሮም ሰዎች 3:10-12ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
ወደ ሮም ሰዎች 3:28
ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና።
ወደ ሮም ሰዎች 3:28ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
7
ወደ ሮም ሰዎች 3:4
እንዲህ አይሁን፤ በቃልህ ትጸድቅ ዘንድ ወደ ፍርድ በገባህም ጊዜ ትረታ ዘንድ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ሰው ሁሉ ውሸተኛ ከሆነ እግዚአብሔር እውነተኛ ይሁን።
ወደ ሮም ሰዎች 3:4ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
သမ္မာကျမ်းစာ
အစီအစဉ်များ
ဗီဒီယိုများ