1
የማርቆስ ወንጌል 2:17
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ኢየሱስም ይህን ሰምቶ፦ “በሽተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፤ እኔም የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ንስሓ ለመጥራት ነው፤” አላቸው።
နှိုင်းယှဉ်
የማርቆስ ወንጌል 2:17ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
የማርቆስ ወንጌል 2:5
ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “ልጄ ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው።
የማርቆስ ወንጌል 2:5ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
የማርቆስ ወንጌል 2:27
ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ሰንበት ለሰው ተሠራ እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም።
የማርቆስ ወንጌል 2:27ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
የማርቆስ ወንጌል 2:4
ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሽባውን ወደ ኢየሱስ ማቅረብ ቢያቅታቸው የቤቱን ጣራ ኢየሱስ ባለበት በኩል ከፍተው ሽባውን ከነአልጋው አወረዱት።
የማርቆስ ወንጌል 2:4ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
የማርቆስ ወንጌል 2:10-11
ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር ለማለት ሥልጣን ያለው መሆኑን እንድታውቁ” ብሎ ሽባውን፥ “ተነሥ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ እልሃለሁ” አለው።
የማርቆስ ወንጌል 2:10-11ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
የማርቆስ ወንጌል 2:9
ሽባውን፥ ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል፤’ ከማለትና፥ ‘ተነሥተህ አልጋህን ተሸከምና ሂድ!’ ከማለት የትኛው ይቀላል?
የማርቆስ ወንጌል 2:9ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
7
የማርቆስ ወንጌል 2:12
ሽባውም ወዲያውኑ ተነሣና አልጋውን ተሸክሞ በሰዎቹ ሁሉ ፊት ወጣ። ስለዚህም ሰዎቹ ሁሉ ተደንቀው እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አይተን አናውቅም እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
የማርቆስ ወንጌል 2:12ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
သမ္မာကျမ်းစာ
အစီအစဉ်များ
ဗီဒီယိုများ