1
ኦሪት ዘፍጥረት 17:1
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ ጌታ ለአብራም ተገለጠለትና፦ “እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፥ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፥
Salīdzināt
Izpēti ኦሪት ዘፍጥረት 17:1
2
ኦሪት ዘፍጥረት 17:5
ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል፥ ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና።
Izpēti ኦሪት ዘፍጥረት 17:5
3
ኦሪት ዘፍጥረት 17:7
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
Izpēti ኦሪት ዘፍጥረት 17:7
4
ኦሪት ዘፍጥረት 17:4
ለብዙ አሕዛብም አባት ትሆናለህ።
Izpēti ኦሪት ዘፍጥረት 17:4
5
ኦሪት ዘፍጥረት 17:19
እግዚአብሔርም አለ፦ “በእውነት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፥ ከእርሱ በኋላ ለዘሩ የዘለዓለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።
Izpēti ኦሪት ዘፍጥረት 17:19
6
ኦሪት ዘፍጥረት 17:8
በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
Izpēti ኦሪት ዘፍጥረት 17:8
7
ኦሪት ዘፍጥረት 17:17
አብርሃምም በግምባሩ ወደቀ፥ ሳቀም፥ በልቡም አለ፦ “የመቶ ዓመት ሰው በውኑ ልጅ ይወልዳልን? ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?”
Izpēti ኦሪት ዘፍጥረት 17:17
8
ኦሪት ዘፍጥረት 17:15
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ “የሚስትህን የሦራን ስም ‘ሦራ’ ብለህ አትጥራ፥ ስምዋ ሣራ ይሆናል እንጂ።
Izpēti ኦሪት ዘፍጥረት 17:15
9
ኦሪት ዘፍጥረት 17:11
የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፥ በእኔና በእናንተ መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።
Izpēti ኦሪት ዘፍጥረት 17:11
10
ኦሪት ዘፍጥረት 17:21
ቃል ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ።”
Izpēti ኦሪት ዘፍጥረት 17:21
11
ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13
የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፥ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያልሆነ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ። በቤትህ የተወለደ በብርህም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆናል።
Izpēti ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13
Mājas
Bībele
Plāni
Video