1
የሉቃስ ወንጌል 17:19
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እርሱንም “ተነሣና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል፤” አለው።
Confronta
Esplora የሉቃስ ወንጌል 17:19
2
የሉቃስ ወንጌል 17:4
በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህ፥ በቀንም ሰባት ጊዜ ‘ተጸጸትሁ’ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ፥ ይቅር በለው።”
Esplora የሉቃስ ወንጌል 17:4
3
የሉቃስ ወንጌል 17:15-16
እነሆም፥ ሲሄዱ ነጹ። ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያወደሰ ተመለሰ፤ እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም ሳምራዊ ነበረ።
Esplora የሉቃስ ወንጌል 17:15-16
4
የሉቃስ ወንጌል 17:3
ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፤ ቢጸጸትም ይቅር በለው።
Esplora የሉቃስ ወንጌል 17:3
5
የሉቃስ ወንጌል 17:17
ኢየሱስም መልሶ “ዐሥሩ አልነጹምን? ዘጠኙስ ወዴት አሉ?
Esplora የሉቃስ ወንጌል 17:17
6
የሉቃስ ወንጌል 17:6
ጌታም አለ፦ “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል፤’ ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር።
Esplora የሉቃስ ወንጌል 17:6
7
የሉቃስ ወንጌል 17:33
ሕይወቱን ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፤ ሕይወቱን የሚያጠፋ ሁሉ ይጠብቃታል።
Esplora የሉቃስ ወንጌል 17:33
8
የሉቃስ ወንጌል 17:1-2
ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ “መሰናክል የግዱን ሳይመጣ አይቀርም፤ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት፤ ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይጠቅመው ነበር።
Esplora የሉቃስ ወንጌል 17:1-2
9
የሉቃስ ወንጌል 17:26-27
በኖኅ ዘመንም እንደሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመንም ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፤ የጥፋት ውሃም መጣ፤ ሁሉንም አጠፋ።
Esplora የሉቃስ ወንጌል 17:26-27
Home
Bibbia
Piani
Video