1
ወደ ሮም ሰዎች 12:2
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
መልካሙንና ደስ የሚያሰኘውን ፍጹም የሆነውንም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ እንድትችሉ አእምሮአችሁን በማደስ ሕይወታችሁ ይለወጥ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉት።
Lee anya n'etiti ihe abụọ
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:2
2
ወደ ሮም ሰዎች 12:1
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:1
3
ወደ ሮም ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ጊዜ ታገሡ፤ ሁልጊዜ ጸልዩ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:12
4
ወደ ሮም ሰዎች 12:21
ስለዚህ ክፉውን ነገር በመልካም ነገር አሸንፍ እንጂ በክፉ ነገር አትሸነፍ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:21
5
ወደ ሮም ሰዎች 12:10
እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ለመከባበርም ተሽቀዳደሙ፤
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:10
6
ወደ ሮም ሰዎች 12:9
ግብዝነት የሌለበት እውነተኛ ፍቅር ይኑራችሁ፤ ክፉውን ነገር ጥሉ፤ መልካሙን ነገር ተከተሉ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:9
7
ወደ ሮም ሰዎች 12:18
የሚቻላችሁ ቢሆን ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የሚያስፈልገውን ሁሉ አድርጉ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:18
8
ወደ ሮም ሰዎች 12:19
ወዳጆቼ ሆይ! ቊጣን ለእግዚአብሔር ተዉ እንጂ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ “የምበቀልና የበቀልንም ብድራት የምከፍል እኔ ነኝ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአል።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:19
9
ወደ ሮም ሰዎች 12:11
ሳትታክቱ የጋለ መንፈስን ተከትላችሁ ጌታን አገልግሉ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:11
10
ወደ ሮም ሰዎች 12:3
ደግሞም እያንዳንዳችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ እምነት መጠን በትሕትና አስቡ እንጂ ከሚገባችሁ በላይ ስለ ራሳችሁ በትዕቢት አታስቡ ብዬ በተሰጠኝ ጸጋ እነግራችኋለሁ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:3
11
ወደ ሮም ሰዎች 12:17
በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አድርጉ እንጂ፥ ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርጉባችሁ፥ እናንተም መልሳችሁ ክፉ ነገር አታድርጉባቸው።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:17
12
ወደ ሮም ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ራሳችሁን ከፍ ከማድረግ ይልቅ ትዕቢትን አስወግዳችሁ ከድኾች ጋር በአንድነት ኑሩ፤ በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:16
13
ወደ ሮም ሰዎች 12:20
ስለዚህ ከመበቀል ይልቅ ጠላትህን ቢርበው አብላው፤ ቢጠማውም አጠጣው፤ ይህን ብታደርግ በዕፍረት እሳት ታቃጥለዋለህ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:20
14
ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁንም መርቁ፤ መርቁአቸው እንጂ አትርገሙአቸው። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
15
ወደ ሮም ሰዎች 12:13
አማኞች ወንድሞችን በችግራቸው እርዱ፤ በእንግድነት የሚመጡትንም ተቀበሉ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:13
16
ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
በአንዱ አካላችን ብዙ ክፍሎች አሉ፤ እያንዳንዱም የአካል ክፍል የተለየ ሥራ አለው። እንዲሁም እኛ ብዙዎች ሆነን ሳለ በክርስቶስ አንድ አካል ነን፤ የአንድ አካል ክፍሎች እንደ መሆናችንም እርስ በርሳችን ተጣምረናል።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
Ebe Mmepe Nke Mbụ Nke Ngwá
Akwụkwọ Nsọ
Atụmatụ Ihe Ogụgụ Gasị
Vidiyo Gasị