1
ኦሪት ዘፀአት 7:1
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እይ፥ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይህ ይሆናል።
Összehasonlít
Fedezd fel: ኦሪት ዘፀአት 7:1
2
ኦሪት ዘፀአት 7:3-4
እኔም የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ፥ ምልክቶቼንና ድንቆቼን በግብጽ ምድር ላይ አበዛለሁ። ፈርዖንም እናንተን አይሰማችሁም፥ እጄንም በግብጽ ላይ አደርጋለሁ፥ ሠራዊቴን፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች፥ በታላቅ የፍርድ ሥራ ከግብጽ ምድር አወጣለሁ።
Fedezd fel: ኦሪት ዘፀአት 7:3-4
3
ኦሪት ዘፀአት 7:5
ግብፃውያንም፥ እጄን በግብጽ ላይ ዘርግቼ የእስራኤልን ልጆች ከመካከላቸው ሳወጣ፥ እኔ ጌታ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”
Fedezd fel: ኦሪት ዘፀአት 7:5
4
ኦሪት ዘፀአት 7:11-12
ፈርዖንም ጠቢባንንና አስማተኞችን ጠራ፤ የግብጽም አስማተኞች ደግሞ በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ። እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፥ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠ።
Fedezd fel: ኦሪት ዘፀአት 7:11-12
5
ኦሪት ዘፀአት 7:17
ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ጌታ እንደሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ እኔ በዓባይ ወንዝ ያለውን ውኃ በእጄ ባለው በትር እመታለሁ፥ ወደ ደምም ይለወጣል።
Fedezd fel: ኦሪት ዘፀአት 7:17
6
ኦሪት ዘፀአት 7:9-10
“ፈርዖን ‘ተአምራትን በማድረግ ማንነታችሁን አሳዩኝ’ ሲላችሁ፥ አሮንን ‘በትርህን ወስደህ እባብ እንዲሆን በፈርዖን ፊት ጣለው’ በለው፥ በትሩም እባብ ይሆናል።” ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ሄዱ፥ ጌታም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት ጣለ፥ እባብም ሆነ።
Fedezd fel: ኦሪት ዘፀአት 7:9-10
Kezdőoldal
Biblia
Olvasótervek
Videók