1
ኦሪት ዘፍጥረት 32:28
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው።
Konpare
Eksplore ኦሪት ዘፍጥረት 32:28
2
ኦሪት ዘፍጥረት 32:26
ከዚህ በኋላ ሰውየው “ሌሊቱ ሊነጋ ስለ ሆነ ልቀቀኝ” አለ። ያዕቆብም “ካልባረክኸኝ አለቅህም” አለው።
Eksplore ኦሪት ዘፍጥረት 32:26
3
ኦሪት ዘፍጥረት 32:24
እርሱ ግን በስተማዶ ለብቻው ቀረ፤ ከዚህ በኋላ ሌሊቱ እስኪነጋ ድረስ አንድ ሰው ሲታገለው ዐደረ።
Eksplore ኦሪት ዘፍጥረት 32:24
4
ኦሪት ዘፍጥረት 32:30
ያዕቆብም “እኔ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቼ እነሆ፥ በሕይወት እገኛለሁ” አለ። በዚህም ምክንያት ያንን ቦታ “ጵንኤል” ብሎ ጠራው።
Eksplore ኦሪት ዘፍጥረት 32:30
5
ኦሪት ዘፍጥረት 32:25
ያ ሰው ያዕቆብን በትግል ማሸነፍ እንዳቃተው ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ መታው፤ ያዕቆብም በሚታገልበት ጊዜ ጭኑ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤
Eksplore ኦሪት ዘፍጥረት 32:25
6
ኦሪት ዘፍጥረት 32:27
ሰውየውም “ስምህ ማን ነው?” አለው። “ስሜ ያዕቆብ ነው” አለው።
Eksplore ኦሪት ዘፍጥረት 32:27
7
ኦሪት ዘፍጥረት 32:29
ያዕቆብም “አንተስ ስምህ ማን ነው?” አለው። ሰውየውም “ስሜን ለማወቅ የምትፈልገው ለምንድን ነው?” አለውና ያዕቆብን ባረከው።
Eksplore ኦሪት ዘፍጥረት 32:29
8
ኦሪት ዘፍጥረት 32:10
እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ።
Eksplore ኦሪት ዘፍጥረት 32:10
9
ኦሪት ዘፍጥረት 32:32
ያዕቆብ ከሰውየው ጋር ሲታገል ሰውየው ሹልዳውን መቶት ስለ ነበር እስራኤላውያን እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን የሹልዳ ሥጋ አይበሉም።
Eksplore ኦሪት ዘፍጥረት 32:32
10
ኦሪት ዘፍጥረት 32:9
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ ሆይ! ልመናዬን አድምጥ፤ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ትውልድ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እዚያም መልካም ነገር እንዲሆንልህ አደርጋለሁ’ ብለኸኝ ነበር።
Eksplore ኦሪት ዘፍጥረት 32:9
11
ኦሪት ዘፍጥረት 32:11
በእኔ ላይ አደጋ በመጣል ሴቶችና ሕፃናት እንኳ ሳይቀሩ ያጠፋናል ብዬ ስለ ፈራሁ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤
Eksplore ኦሪት ዘፍጥረት 32:11
Akèy
Bib
Plan yo
Videyo