1
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ዓላማውም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
Usporedi
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39
ይህንን ተረድቼአለሁ፤ ሞትም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ገዢዎችም ቢሆኑ፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ጥልቀትም ቢሆን፥ ሌላ ፍጥረትም ቢሆን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ይረዳናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ያማልድልናል፤
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31
እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1
ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም።
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37
በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18
የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ወደ ፊት ለእኛ ከሚገለጥልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም ዋጋ እንደሌለው እቆጥረዋለሁ።
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18
9
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? መከራ ወይስ ሥቃይ፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ረሃብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ አደጋ፥ ወይስ ሰይፍ?
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35
10
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27
ልቦችንም የሚመረምረው እርሱ የመንፈስ ሐሳብ ምን እንደሆነ ያውቃል፥ ምክንያቱም መንፈስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ያማልዳልና።
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27
11
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ፥ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14
12
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5
እንደ ሥጋ የሚኖሩ አእምሮአቸው የሥጋን ነገር እንዲያስብ ያደርጋሉና፥ እንደ መንፈስ የሚኖሩ ግን አእምሮአቸው የመንፈስን ነገር እንዲያስብ ያደርጋሉ።
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5
13
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው እርሱ፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
14
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈሱ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክርልናል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ከእርሱ ጋር የክብሩ ተካፋዮች እንድንሆን ከእርሱ ጋር መከራ ብንቀበል የእግዚአብሔር ወራሾችና ከክርስቶስም ጋር አብረን ወራሾች ነን።
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17
15
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7
ስለ ሥጋ ማሰብ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን ነው፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም አይችልም፥
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7
16
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19
ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በታላቅ ናፍቆት ይጠባበቃልና።
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19
17
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22
እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ አብሮ በመቃተትና በምጥ ሥቃይ እንደሚኖር እናውቃለንና።
Istraži ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22
Početna
Biblija
Planovi
Filmići